Search
 

Amharic

Fri, 12/01/2017 - 15:53 -- michael.mishani

የትምህርት ዓመት 2021-2022 የምዝገባ መመሪያ እና ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎች

DCPS፣ ለቤተሰቦቻችን ምዝገባን በመክፈቱ ደስታ እየተሰማው እና አዲስ ተማሪዎችን ወደ ማህበረሰባችን እንኳን ደህና መጣችሁ ይላል! በDCPS ትምህርት ቤቶች ውስጥ፣ ለትምህርት ዓመት 2021-2022 (SY21-22) የኤሌክትሮኒክ እና በአካል-ተገኝቶ (in-person) ምዝገባን ለማከናወን፤ ከአርብ ኤፕሪል (April) 2 ቀን 2021 ጀምሮ የሚገኝ ይሆናል። በኤሌክትሮኒክ ለመመዝገብና ሂደቱን ለማጠናቀቅ፣ ወላጆች የኢሜል አድራሻ ያስፈልጋቸዋል። የኤሌክትሮኒክ የምዝገባ ጥራዝን (electronic enrollment packet) እዚህ ከኮምፒውተር፣ ከስማርትፎን ወይም ከሌላ የሞባይል ዲቫይስ አማካኝነት፣ መገኘት ይችላል። 

ከወዲሁ፣ ቀደም-ብለን የበልግ (fall) ወቅትን ስንመለከት፤ በመጪው SY21-22 ውስጥ፣ DCPS በአካል ተገኝቶ (in-person) መማርን ለተማሪዎቻችን ለመስጠት አስቧል። በአካል ተገኝቶ (in-person) እና በርቀት በምናባዊ (virtual) መማር ላይ፣ ስለ ሁለቱም፤ አዳዲስ መረጃዎችን፣ በdcpsreopenstrong.com ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።

ለልጅዎ የSY21-22 ምዝገባን ሞልተው ያጠናቁ

  1. ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ያንብቡ። 
  1. እንደአስፈላጊነቱ ለመጫን (upload ለማድረግ)፤ አስፈላጊ-የሆኑ አጋዥ የመረጃ-ስነዶችን (supporting documentation) መሰብሰብ

ወደ ማንኛውም የDCPS ትምህርት ቤት አዲስ ለሆኑ

  • አንድ የዕድሜ ማረጋገጫ ሰነድ  – ምሳሌዎቹ የሚያካትቱት፡ የልደት ሰርተፊኬት፣ የሆስፒታል መዝገቦች፣ የቀድሞ የትምህርት ቤት መዝገቦች፣ ፓስፖርት፣ ወይም የጥምቀት ሰርተፊኬት
  • የዲሲ የነዋሪነት ማረጋገጫ  – ተቀባይነት ያላቸውን ሰነዶች እና ማረጋገጫ ዘዴዎችን፣ ሙሉ ዝርዝሩን ለማግኘት፤ የዲሲ የነዋሪነት ማረጋገጫ ቅጽንይመልከቱ።

አሁን ወደሚማሩበት የDCPS ትምህርት ቤት ለሚመለሱ 

  • የዲሲ የነዋሪነት ማረጋገጫ  – ተቀባይነት ያላቸውን ሰነዶች እና ማረጋገጫ ዘዴዎችን፣ ሙሉ ዝርዝሩን ለማግኘት፤ የዲሲ የነዋሪነት ማረጋገጫ ቅጽንይመልከቱ።
  1. SY21-22 የኤሌክትሮኒክ የማስገቢያ የምዝገባ ጥራዝ (packet)ሞልተው ያጠናቅቁ። *ለየብቻቸው-የሆኑ ቅጾችም፣ እዚህ መገኘት ይችላሉ
    • ምዝገባውን በኤሌክትሮኒክ ወይም በአካል ተገኝቶ (in-person) ለማጠናቀቅ እርዳታ ካስፈለገዎ፣ ትምህርት ቤትዎን ያነጋግሩ
    • ለኤሌክትሮኒክ ምዝገባ፣ በክልል-ወሰን ውስጥ (in-boundary) ትምህርት ቤቶች እና የዲሲ የነዋሪነት ማረጋገጫ ቅጽ ላይ የሚመሩ ቪዲዮዎች፤ በቅርብ ጊዜ የሚገኙ ይሆናሉ 

እባክዎን የምዝገባ ፖሊሲያችንን ይመልከቱ። አሁንም፣ ጥያቄዎች አሏችሁ? አነጋግሩን

ትምህርት ቤትዎን ፈልገው ያግኙ

የ‘My School DC’ ሎተሪ

ስለ’My School DC’ ሎተሪ

የ‘My School DC’ ሎተሪ፤ በኮሎምብያ ዲስትሪክት ውስጥ በሚገኙ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች፣ የሚከተሉትን ጨምሮ፤ ልጆቻቸውን ማስመዝገብ ለሚፈልጉ ቤተሰቦች፣ የትምህርት ቤት መምረጫ አገልግሎትን ይሰጣል: 

  1. በአሁኑ ጊዜ፤ ቅድመ-ትምህርት ቤት (PK3) እና ቅድመ መዋዕለ-ሕፃናት (PK4)፣ ውስጥ የማይማሩ።
  2. በአሁኑ ጊዜ፤ ከK-12 ከክልል ወሰን ውጪ (Out-of-Boundary) ትምህርት ቤቶች፣ የማይማሩ።
  3. በአሁኑ ጊዜ፤ ከተማአቀፍ ትምህርት ቤቶች፣ የማይማሩ።
  4. በአሁኑ ጊዜ፤ ተመራጭ (Selective) ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ የማይማሩ።

አሁን በሚገኙበት፣ በክልል ወሰን ውስጥ (in-boundary) ወይም በአዘዋዋሪ-ንድፍ (Feeder Pattern) ትምህርት ቤት ውስጥ ለመማር፣ የ‘My School DC’ ሎተሪ ማመልከቻ አያስፈልግምበክልል ወሰን ውስጥ (in-boundary) እና አዘዋዋሪ (feeder) ትምህርት ቤቶችዎን ለይቶ ማወቅ።

እንዴት ማመልከት ይቻላል

ለማመልከት፣ የ‘My School DC’ ሎተሪ ድህረ-ገጽን በmyschooldc.org ይጎብኙ።

አነጋግሩን! 

ተጨማሪ የምዝገባ እርዳታ ያስፈልግዎታል? ጥያቄዎችዎ፤ በመጀመሪያ ቋንቋዎ እንዲመለስልዎ ከፈለጉ፣ እባክዎን ወደ [email protected] ኢሜል ይላኩ ወይም የዲሲ የሕዝብ ትምህርት (DCPS)፣ የቋንቋ እገዛ ማግኛ ክፍል (Language Acquisition Division)ን በ (202) 671-0750 ደውለው ያነጋግሩ።

ለኤሌክትሮኒክ ምዝገባ፣ በክልል-ወሰን ውስጥ (in-boundary) ትምህርት ቤቶች እና የዲሲ የነዋሪነት ማረጋገጫ ቅጽ ላይ የሚመሩ ቪዲዮዎች፤ እዚህ ይገኛሉ: